Search

ምክር ቤቱ የቋሚ ኮሚቴዎች ዕጩ አመራር እና አባላትን ምደባ አስመልክቶ የቀረበውን የውሳኔ ሐሳብ መርምሮ አጸደቀ

ሓሙስ ጥቅምት 05, 2019 75

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ስብሰባው፣ የቋሚ ኮሚቴዎች ዕጩ አመራር እና አባላትን ምደባ አስመልክቶ የቀረበውን የውሳኔ ሐሳብ መርምሮ አጽድቋል።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አሕመድ ሽዴ ባቀረቡት የውሳኔ ሐሳብ፣ በእጩዎች የአመራረጥ ሂደት ከመንግሥት ተጠሪ እና ከፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ጋር ሰፊ ውይይት የተደረገበት መሆኑን ገልጸው፣ ብዝኃነትን፣ ብቃትን፣ የሥራ ልምድን፣ በምክር ቤቱ መቀመጫ ያላቸውን የተፎካካሪ ፓርቲዎች ታሳቢ ያደረገ እንዲሁም አዲስ እና ነባር አባላትን ያካተተ ለማድረግ ጥረት መደረጉን አንስተዋል።

በዚህም መሠረት፦

• ቀነአ ያደታ (ዶ/ር)፦ የሕግና ፍትሕ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ

• አቶ ታርጃት ደቦል፦ የሕግና ፍትሕ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ

• አቶ መለሰ መና፦ የግብርና ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ

• እሱባለው መብራት (ዶ/ር)፦ የግብርና ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ

• ወ/ሮ እጸገነት መንግሥቱ፦ የዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ

• አቶ ጫላ ለሚ፦ የዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ

• አቶ ሰለሞን ላሌ፦ የንግድ፣ ባሕልና ቱሪዝም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ

• አቶ ጣሂር መሐመድ፦ የንግድ፣ ባሕልና ቱሪዝም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ

• አቶ ደሳለኝ ወዳጄ፦ የኢንዱስትሪ እና ማዕድን ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ

• ወ/ሮ ወላይቴ ኢቶ፦ የኢንዱስትሪ እና ማዕድን ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ

• ወ/ሮ ወሰነች ቶማስ፦ የብሔራዊ ስትራቴጂ፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ

• ወ/ሮ ዝናሽ ጸጋዬ፦ የብሔራዊ ስትራቴጂ፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ

• ዲማ ኖጎ (ዶ/ር)፦ የውጭ ግንኙነት እና ሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ

• ፈትሒ ማሕዲ (ዶ/ር)፦ የውጭ ግንኙነት እና ሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ

• ወ/ሮ የሺሐሳብ ጸጋው፦ የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ

• እሸቱ ተመስገን (ዶ/ር)፦ የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ

• አቶ አለማየሁ እጅጉ፦ የከተማ መሠረተ ልማት እና ሎጂስቲክስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ

• አወቀ አምዛዬ (ዶ/ር)፦ የከተማ መሠረተ ልማት እና ሎጂስቲክስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ

• አብርሃም አለማየሁ (ዶ/ር)፦ የመንግሥት ወጪ፣ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ

• ወ/ሮ አራሬ ሞሲሳ፦ የመንግሥት ወጪ፣ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ

• አቶ ንጋቱ ወልዴ፦ የውኃ፣ መስኖ፣ ቆላማ አካባቢ እና አካባቢ ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ

• ወ/ሮ ነፊሳ አልማህዲ፦ የውኃ፣ መስኖ፣ ቆላማ አካባቢ እና አካባቢ ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ

• ወ/ሮ መሰረት ኃይሌ፦ የጤና፣ ማኅበራዊ ልማት እና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ

• ወ/ሮ ጀሚላ ሲምቢሮ፦ የጤና፣ ማኅበራዊ ልማት እና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ

• ነገሪ ሌንጮ (ዶ/ር)፦ የሰው ሀብት ልማት፣ ሥራ ስምሪት እና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ

• ወ/ሮ ዘሃራ ሰምሬ፦ የሰው ሀብት ልማት፣ ሥራ ስምሪት እና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ ሆነው ተሰይመዋል።

ምክር ቤቱ የቋሚ ኮሚቴዎች ዕጩ አመራርና አባላትን ምደባ አስመልክቶ የቀረበውን የውሳኔ ሐሳብ፤ ውሳኔ ሐሳብ ቁጥር 4/2019 ዓ.ም. አድርጎ በሙሉ ድምፅ አጽድቆታል።

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: