Search

በአማራ ክልል በተለያዩ ከተሞች ለጀግናው የሀገር መከላከያ ሠራዊት ሕዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ እየተደረገ ነው

ቅዳሜ ጥቅምት 07, 2019 32

ለጀግናው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የሀገርን ዳር ድንበር ለማስከበር እያደረገ ላለው ታላቅ ተጋድሎ እና ሕግ ለማስከበር እያከናወነ ለሚገኘው አመርቂ ውጤት አጋርነታቸውን ለማሳየት፣ በአማራ ክልል በተለያዩ ከተሞች ከጥዋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ ሕዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።

በክልሉ በሰሜን ጎንደር በተለያዩ ከተሞች፣ በጎንደር ከተማ፣ በደባርቅ ከተማ እና በሌሎችም ከተሞች እንዲሁም በሰሜን ወሎ ዞን፣ በወልዲያ ከተማ፣ በፍላቂት ገረገራ ከተማ አስተዳደር እና በመቄት ወረዳ፣ በሠቆጣ እና ወረታ ከተሞች፣ በደብረ ታቦር ከተማ የድጋፍ ሰልፉ እየተካሄደ ነው።

በሕዝባዊ ሰልፉም የጀግናውን የሀገር መከላከያ ሠራዊት ሕግ የማስከበር ዘመቻ እና የሀገርን ሉዓላዊነት ለማስከበር እየተከናወኑ ያሉ የጀግንነት ሥራዎችን በመደገፍ፦

“የኅብረ ብሔራዊ ወንድማማችነት እና እኅታማችነት አርማ የሆነውን የሀገር መከላከያ ሠራዊታችንን እንደግፋለን!”

“የባሕር በር ባለቤትነታችን በልጆቿ መሥዋዕትነት ዕውን ይሆናል!”

“የሀገራችንን ሰላም ለማወክ ከታሪካዊ ጠላቶቻችን ጋር የተሰለፉ ኃይሎችን በጽኑ እናወግዛለን!”

“የአካባቢያችን፣ የክልላችን እና የሀገራችን ሰላም በጋራ ጥበቃ ይረጋገጣል!”

የሚሉ እና ሌሎች መልእክቶች በሰልፉ እየተንጸባረቁ ይገኛሉ።

በራሔል ፍሬው እና በተስፋሁን ደስታ

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: