Search

“የክልላችን ሕዝብ እውነተኛ ፍላጎት ሰላም፣ የሕግ የበላይነት እና ልማት መሆኑን በአደባባይ አረጋግጧል”፦ ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ

ቅዳሜ ጥቅምት 07, 2019 57

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደ፣ የክልሉ ሕዝብ ለሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ ለክልሉ የፀጥታ አካላት ተጋድሎ እና ለኢትዮጵያ ሀገራዊ መጽናት ያለውን ደጋፊነት በአደባባይ ወጥቶ በተግባር ማረጋገጡን ገለጹ።

ርዕሰ መስተዳድሩ ባስተላለፉት መልዕክት፣ የሕዝቡ እውነተኛ እና አንጡራ ፍላጎት ሰላም፣ የሕግ የበላይነት እና ልማት የተረጋገጠበት ሀገር እና ክልል መፍጠር መሆኑን በዛሬው ዕለት በተካሄደው ታላቅ ትዕይንተ-ሕዝብ ማረጋገጡን ጠቁመዋል። አክለውም ይኸው ሰልፍ ሕዝቡ ለሀገር አንድነት ያለውን የማይናወጥ አቋም በድጋሜ ያሳየበት መሆኑን ገልጸዋል።

ኢትዮጵያውያን አንድነታቸው ክብራቸው፣ ጀግንነታቸው መጠሪያቸው እንዲሁም ነፃነታቸው መለያቸው መሆኑን ያነሱት አቶ አረጋ ከበደ፣ ይህ ነፃነት በየዘመናቱ በነበሩ ትውልዶች በከበረ መስዋዕትነት የተገኘ ድል እንደሆነ አውስተዋል።

ታሪክን በኅብረት ጠብቆ፣ ነፃነትን አጽንቶ የበለጸገች እና የተከበረች ሀገር ለመጪው ትውልድ ለማስረከብ በጋራ መሥራት እንደሚገባ በመጠቆም፣ የክልሉ ሕዝብ ለሰላም መሥፈን እና ለሕግ የበላይነት መከበር ላሳየው የጸና አቋም እና ለሰጠው ከፍተኛ ድጋፍ ላቅ ያለ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: