Search

የሲዳማ ክልል የ2019 በጀት 55 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ሆኖ ጸደቀ

ቅዳሜ ጥቅምት 07, 2019 33

የሲዳማ ክልል ምክር ቤት 7ኛ ምርጫ ዙር 1ኛ ሥራ ዘመን 1ኛ አስቸኳይ ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤው፣ የክልሉን የ2019 በጀት 55 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር አድርጎ አጽድቋል።

የበጀት ዕቅዱን ለምክርቤቱ ያቀረቡት የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እና የፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ ዳዊት ሀዬሶ (ዶ/ር) በጀቱ በዋናነት በክልሉ በድህነት ቅነሳ፣ በመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች ግንባታ፣ በዘላቂ የልማት ግቦች እና በተያያዥ ቁልፍ ተግባራት ላይ የሚውል መሆኑን ዶክተር ዳዊት በዝርዝር አስረድተዋል።

የቀረበውን በጀት የምክር ቤቱ አባላት በሙሉ ድምፅ አፅድቀዋል።

በአስረሳው ወገሼ

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: