Search

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የሞዛምቢክ አቻውን 1 ለ 0 አሸነፈ

ዓርብ ኅዳር 04, 2019 134

በ2027 አፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ በምድብ አስር ሦስተኛ መርኃ ግብር ማፑቶ ላይ በዚምፔቶ ስታዲየም ሞዛምቢክን የገጠመው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን 1 ለ 0 አሸንፏል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከ48 የማጣሪያው ተሳታፊ ቡድኖች ብቸኛ ያደረገውን ግብ ያለማስቆጠር ችግር በቀረፈበት ጨዋታ፣ ብቸኛዋን የማሸነፊያ ግብ 87ኛው ደቂቃ ላይ ከነዓን ማርክነህ አስቆጥሯል።

የማጣሪያውን የመጀመሪያ ግብ እና የመጀመሪያ ሶስት ነጥብ ያገኘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን፣ ደረጃውን ወደ 3ኛ አሻሽሏል።

ምድቡን ሴኔጋል በሰባት ነጥብ ስትመራ፣ ሞዛምቢክ በአራት ነጥብ ሁለተኛ እንዲሁም ሶስት ነጥብ ይዛ ከኢትዮጵያ በግብ ክፍያ ያነሰችው ሱዳን ግርጌ ላይ ተቀምጣለች።

 

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የመልሱን ጨዋታ ቀጣይ ሳምንት ማክሰኞ በባህርዳር ስታዲየም ያደርጋል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: