Search

በአፍሪካ የፖለቲካ ፓርቲዎች በሕዝብ እና በተቋማት መካከል ድልድይ በመሆን ማገልገል አለባቸው፡- መሀሙድ አሊ ዩሱፍ

ዓርብ ጥቅምት 27, 2019 86

በአፍሪካ የፖለቲካ ፓርቲዎች በሕዝብ እና በተቋማት መካከል ድልድይ በመሆን ማገልገል እንዳለባቸው የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሀሙድ አሊ ዩሱፍ አስገነዘቡ።

2ኛው የአፍሪካ ፖለቲካ ፓርቲዎች ጉባዔ “ለዕድገት መምራት፦ የፖለቲካ ፓርቲዎች እንደ የአፍሪካ መጻኢ የኢኮኖሚ መሐንዲሶች” በሚል መሪ ሐሳብ በዓድዋ ድል መታሰቢያ እየተካሄደ ይገኛል።

የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሀሙድ አሊ ዩሱፍ በዚህ ወቅት፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለአፍሪካ ለውጥ ለፈጠሩት የፖለቲካ ራዕይ ምስጋና አቅርበዋል።

የአፍሪካ ሕብረት አጀንዳ 2063 የዴሞክራሲ አስተዳደር ሥርዓት በአሕጉሪቱ የተቀናጀ የፖለቲካ ሥርዓት መፍጠር እንዳለባቸው መደንገጉን ገልጸው፣ የአፍሪካ የፖለቲካ ፓርቲዎች በፖሊሲ የተደገፈ የሕዝብ አገልግሎት መስጠት አለባቸው ብለዋል።

መሪ ፓርቲዎች ህገ መንግሥታዊ አስተዳደር የመነጨ ተዓማኒ ምርጫ ማዘጋጀት እንዳለባቸው ገልጸው፣ በፓርቲዎች መካከል ውይይትና ንግግር ወሳኝ መሆኑን አመላክተዋል።

በአፍሪካ ሥልጣንን ኢ-ሕገ መንግሥታዊ በሆነ መንገድ ለመቆጣጠር መሞከር ተገቢ አይደለም ያሉት የኮሚሽኑ ሊቀ መንበር፣ ይህም ለግጭትና አለመረጋጋት የሚጋብዝ በመሆኑ የአፍሪካ ሕብረት ኢ-ሕገ መንግሥታዊ አካሄዶችን በፅኑ እንደሚያወግዝ አስገንዝበዋል።

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: