የኢትዮጵያ የገንዘብ ሚኒስትር እና የCOP32 ዋና ተደራዳሪ ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) በቱርክዬ አንታሊያ እየተካሄደ ካለው የኮፕ 31 ጉባኤ ጎን ለጎን፣ ከፈረንሳይ የልማት ኤጀንሲ ስራ አስፈፃሚ ክሪስቶፍ ለኩርቲየር ጋር ተወያይተዋል።
ውይይታቸውም ከኢትዮጵያ ጋር ያለ አጋርነትን ይበልጥ ለማጠናከር እና የCOP32 ጉዳዮች ላይ በቀጣይ ለመሥራት መሆኑን ከኮፕ32 ኢትዮጵያ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።
የሰው ዘር መገኛ፣ የፅናት እና የተስፋ ምድር የሆነችው ኢትዮጵያ ዓለም አቀፉን አየር ንብረት ጉባኤ ለማስተናገድ የምታደርገውን ሀገራዊ እንቅስቃሴ በተመለከተ ሙሉ እና ትክክለኛ የጉባኤውን መረጃዎች ከምንጩ ለማግኘት ሁልጊዜም የኮፕ-32 ይፋዊ ድረ-ገጽ https://cop32ethiopia.et/ ይጠቀሙ።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: