በኢትዮጵያ መንግሥት እና በተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ ትብብር የተጀመረው ሀገራዊ የዲጂታል ክህሎት ማሳደጊያ ፕሮግራም፣ በመጀመሪያ አቅዶት የነበረውን የ5 ሚሊዮን ወጣቶች ስልጠና ግብ ወደ 7 ሚሊዮን አድርሷል።
በወጣቶች ዘንድ የታየው ከፍተኛ የስልጠና ፍላጎት እና የፈጣን ምዝገባ ምላሽ ነው ቁጥሩን ወደ 7 ሚሊየን እንዲያድግ ያስቻለው።
ተሳታፊዎች በፕሮግራሚንግ፣ በዳታ ሳይንስና ትንተና፣ በአንድሮይድ መተግበሪያ ልማት እንዲሁም በሰው ሰራሽ አስተውሎት መሠረታዊ እውቀት ላይ ስልጠና ያገኛሉ። ስልጠናዎቹ በኦንላይን የሚሰጡ ሲሆን፣ በስልክ ወይም በኮምፒውተር መከታተል ይቻላል። ይህም ሰልጣኞች በያሉበት ሆነው ዘመናዊውን የዲጂታል ክህሎት በቀላሉ እንዲቀስሙ አስችሏቸዋል፡፡
ስልጠናውን በተሳካ ሁኔታ የሚያጠናቅቁ ተሳታፊዎች የክህሎት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ያገኛሉ፤ ይህም ወጣቶች በቴክኖሎጂ ዘርፍ የሥራ እድሎችን እንዲያስፋፉ እና በዲጂታል ኢኮኖሚው ውስጥ የበለጠ እንዲሳተፉ ያግዛል።
ኢኒሼቲቩ ከስልጠና ባሻገር ወጣቶች በፍሪላንሲንግ፣ በቴክኖሎጂ ሥራ ፈጠራ እና በዲጂታል አገልግሎቶች የገቢ እድሎችን እንዲፈጥሩ ማበረታታትንም ያካትታል።
የ7 ሚሊዮን ኮደሮች ኢኒሼቲቭ በሀገራችን የዲጂታል ክህሎት ማስፋፋትን በማጠናከር ወጣቶችን ከቴክኖሎጂ ዘርፍ ጋር ለማቀራረብ የሚያስችል ትልቅ እድል ነው።
በሲሳይ መንግሥቱ
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: