የዛሬውን የእመርታ ቀን ስናከብር የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር የኢትዮጵያን ግብርና ከዝናብ ጥገኝነት በማላቀቅ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ያስመዘገበውን ተቋማዊና መዋቅራዊ ድል በማበሰር ነው።
የመስኖ ዘርፉ ላለፉት በርካታ ዓመታት በተበታተነ አወቃቀር ሲመራ የቆየ ቢሆንም፣ በአዋጅ ቁጥር 1263/2014 ተቋሙ በይፋ አዲስ መዋቅር ይዞ እንዲደራጅ ተደርጓል።
ይህም ለዘርፉ ግልጽ አሠራርን፣ ተጠያቂነትን፣ የፋይናንስ ጥንካሬንና የበጀት ነፃነትን በመፍጠር መንግሥት በየዓመቱ ከ20 ቢሊዮን ብር በላይ ቀጥተኛ በጀት እንዲመድብለት አስችሏል።
ይህ ተቋማዊ እመርታ ለ20 ዓመታት በግንባታ መጓተት ሲሰቃዩ የነበሩትን የመገጭ እና የአርጆ ዲዴሳ ፕሮጀክቶች ሥራ ለማፋጠን ያስቻለ ሲሆን፤ እንደ ከሰም፣ ተንዳሆ፣ ታችኛው ርብ፣ ጊዳቦ፣ ወልመል፣ ቄጦ፣ ፊና እና ጎዴ ያሉ ግዙፍ ፕሮጀክቶች ሙሉ በሙሉ ተጠናቀው ለአገልግሎት እንዲበቁ አድርጓል።
ይህ ውጤትም የኢትዮጵያን የመስኖ ሽፋን ከ490 ሺህ ሄክታር ወደ 2.7 ሚሊዮን ሄክታር ያሳደገ ታሪካዊ ስኬት ማስመዝገብ ተችሏል።
ሚኒስቴሩ በቆላማና አርብቶ አደር አካባቢዎች የዳመና ማበልጸጊያ ቴክኖሎጂዎችን፣ የመጠጥ ውሃ፣ የትምህርትና ጤና ተቋማትን እንዲሁም የእንስሳት ሕክምና ማዕከላትን በመገንባት የዜጎችን ህይወት በቀጥታ የሚቀይሩ ስራዎችን አከናውኗል።
ኢትዮጵያ የመረጠችው ውሳኔ ዝናብ የሚያመጣውን ብቻ መጠበቅ ሳይሆን ውሃን በመቆጣጠር የምግብ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ በመሆኑ የእመርታ ቀን ይህንን አዲሱን የታሪክ ማዕበል በግልጽ ያበስራል።
በንብረቴ ተሆነ
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: