የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሕዝብን የልማት ጥያቄዎች ለመመለስ በትኩረት እንደሚሠራ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) ተናገሩ።
ርዕሰ መስተዳድሩ በወላይታ ሶዶ ከተማ በመገኘት ሥራቸውን በይፋ የጀመሩ ሲሆን፣ በቀጣይ በትኩረት በሚሠሩ ጉዳዮች ዙሪያ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በዚህም የሕዝቡን ፍትሐዊ ተጠቃሚነት ከማሳደግ ባለፈ ክልሉን የሰላምና የብልጽግና ተምሳሌት ለማድረግ በትጋት እንደሚሠራ ገልጸዋል።
ፍትህና ዘላቂ ሰላም፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ልማት፣ የመሠረተ ልማት ተደራሽነትና መልካም አስተዳደርን ማምጣት እንዲሁም የመግባባት ዴሞክራሲን ማጎልበት በሚያስችሉ ተግባራት ላይ በርብርብ እንደሚሠራ ጠቁመዋል።
ክልሉ እምቅ የልማት አቅም ያለው መሆኑን ጠቅሰው፣ ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ፖሊሲው የፈጠረውን ምቹ ሁኔታ በመጠቀም የክልሉን ሀብት ወደ ተጨባጭ ኢኮኖሚያዊ አቅም ለመቀየር ይሠራል ብለዋል።
በዚህም ተመደመር መንግሥትን የብዝኃ ዘርፍ ኢኮኖሚ ልማት አቅጣጫን በመከተል መዋቅራዊ ሽግግር ለማምጣት በቅንጅት እንደሚሠራም አመላክተዋል።
በተመስገን ተስፋዬ
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: