Search

የተፈጥሮ ውበቷን በኮሪደር ልማት ያስጌጠችው ወቧ ባሕር ዳር

ቅዳሜ ኅዳር 19, 2019 146

በጣና ሐይቅ ዳርቻ የምትገኘው እና በዘንባባ ዛፎቿ፣ በሰላማዊ መንፈሷ እንዲሁም በታሪካዊነቷ የምትታወቀው ባሕር ዳር፣ በኮሪደር ልማት ሥራዎች ታጅባ ይበልጥ ውብ እና ለነዋሪዎችም ሆነ ለጎብኝዎች ምቹ እየሆነች ትገኛለች።

የከተማዋን ተፈጥሯዊ ጸጋ ከዘመናዊ የከተማ ልማት ጋር በማቀናጀት የተሰሩት የኮሪደር ልማት ሥራዎች፤ የእግረኛ እና የብስክሌት መንገዶችን፣ የመዝናኛ ስፍራዎችን እንዲሁም የመብራት እና የውበት ሥራዎችን በማካተት የባሕር ዳርን ገጽታ በአዲስ መልክ አድምቀውታል።

የሐይቁን ነፋሻማ አየር እየተቀበሉ በንጹህ እና በተደራጀ መንገድ መንቀሳቀስ መቻሉ፣ የከተማዋን የቱሪስት መስህብነት ከማሳደግ ባለፈ የነዋሪዎችን የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ እና የመዝናኛ ጊዜ ይበልጥ አሳምሮታል።

በተለይም ምሽት ላይ በደመቁ መብራቶች እና በተስተካከሉ ምቹ ስፍራዎች ስትታይ ባሕር ዳር፣ የተፈጥሮ ውበት እና የልማት ውጤት የተዋሃዱባት ድንቅ ከተማ መሆኗን በግልጽ ያሳያል።

በለሚ ታደሰ

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: