Search

እንደ ቢሾፍቱ አውሮፕላን ማረፊያ ያለ በተቀናጀ መንገድ የሚመራ ውስብስብ ፕሮጀክት የትም የለም፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ሓሙስ ኅዳር 17, 2019 105

የቢሾፍቱ አውሮፕላን ማረፊያ ፕሮጀክት የመሬት ጠረጋ ዝግጅት በቅርቡ እንደሚጠናቀቅ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በ7ኛው የኢፌዴሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ ተገኝተው በሰጡት ማብራሪያ፣ የቢሾፍቱ አውሮፕላን ማረፊያ ፕሮጀክት ቀጣይ ምዕራፍ የሆነውን የአውሮፕላን መንደርደሪያ ለመገንባት በአሁኑ ወቅት በጨረታ ሂደት ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

በዚህም በሚቀጥሉት አንድ እና ሁለት ወራት ውስጥ የጨረታው ውጤት እንደሚታወቅ ጠቁመዋል።

በአንድ ጠባብ ቦታ ላይ ከ4 ሺህ በላይ ተሽከርካሪዎች እና ማሽነሪዎች በሰው ሠራሽ አስተውሎት ታግዘውና ተናብበው ሲሠሩ ማየት አስገራሚ መሆኑን አንስተዋል።

የምክር ቤቱ አባላትም ይህን አስተማሪ የሆነ ፕሮጀክት ሄደው እንዲጎበኙት መክረዋል።

ፕሮጀክቱን መጀመር አትችሉም ተብሎ የነበረ ቢሆንም፣ ሥራው መጀመሩ ማሳካት እንደሚቻል የታየበት መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።

በለሚ ታደሰ

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: