Search

የኮሪደር ልማቱ ከተሞችን ከመኖሪያነት ባለፈ የኢኮኖሚ ማዕከል አድርጓቸዋል - የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር

እሑድ ጥቅምት 01, 2019 69

የአፍሪካ ከተሞች ከንቲባዎች ፎረም በውበቷና ፈጣን ዕድገቷ በምትታወቀው ቢሾፍቱ ከተማ በደመቀ ሁኔታ እየተካሄደ ይገኛል።

ከ4 ዓመታት በፊት የተመሠረተውና 55 የአፍሪካ ከተሞች ከንቲባዎችን በአባልነት ያቀፈው ይህ ፎረም፤ ከተሞች በዲጂታል አሠራር፣ በከተሞች ማስዋብ እንዲሁም በኢኮኖሚ ግንባታ ዙሪያ ልምድና ተሞክሮ የሚለዋወጡበት መድረክ ነው።

የዘንድሮው መድረክ ከፍተኛ የከተማ ልማትና ለውጥ ባስመዘገበችው ቢሾፍቱ ከተማ እየተካሄደ የሚገኝ ሲሆን፣ የፎረሙ ተሳታፊዎች በከተማዋ የተከናወኑ የኮሪደር ልማት ሥራዎችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።

በከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር የፖሊሲ ዳይሬክተርና የኢትዮጵያ ከተሞች ፕሮግራም መሪ ያሬድ ተሾመ (ዶ/ር) በፎረሙ እንደገለጹት፤ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ሀገር በቀል የከተማ ልማት ሥራዎች ከተሞችን ከመኖሪያነት ባሻገር ዋና የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ማዕከል እንዲሆኑ አድርገዋቸዋል።

አክለውም፣ የኮሪደር ልማትን ጨምሮ በየደረጃው የተከናወኑ ከተማ ተኮር ልማቶች የሥራ ዕድል ፈጠራን ማዕከል አድርገው የተተገበሩ መሆናቸውን ገልጸው፤ በዚህ ሴክተር የተመዘገቡ ስኬቶች የኢትዮጵያ ከተሞችን ለአፍሪካ አህጉር ምሳሌ ያደረጉ ናቸው ብለዋል።

ከዛሬ ጀምሮ እስከ ጥቅምት 5 ቀን 2017 ዓ.ም የሚቆየው ይህ አህጉራዊ ፎረም፣ ከተሞች የሥራ ተሞክሯቸውን የሚያጋሩበትን እና እርስ በርስ የሚማማሩበትን ዕድል ፈጥሯል።

በባዬ ሙላት

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: