Search

የኢትዮጵያ ሁለንተናዊ የዝግጁነት ጉዞ፡- ከተቋማዊ ሪፎርም እስከ አስተማማኝ የአየር ደኅንነት

ረቡዕ ጥቅምት 04, 2019 71

ኢትዮጵያ ብሔራዊ ግቦቿን ለማሳካትና ተግዳሮቶችን ለመቋቋም የሚያስችላትን ሁለንተናዊ የዝግጅት ሥርዓት በመገንባት ላይ ትገኛለች።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመደመር መንግሥት ምስረታ ወቅት እንደገለጹት፤ ሀገራችንን በተለያዩ ዘርፎች የማትበገርና ጠንካራ የማድረግ ሥራዎች በትኩረት እየተከናወኑ ይገኛሉ።

ኢኮኖሚው ዘርፍም ቢሆን፣ ሀገራችን ማንኛውንም የተፈጥሮም ሆነ የሰው ሰራሽ አደጋዎች እንዲሁም የኢኮኖሚ ጫናዎችን የመቋቋም አቅሟ እንዲጎለብት መዋቅራዊ ማሻሻያዎች እየተደረጉ ነው።

በሌላ በኩል ከአየር ንብረት ለውጥና ተፈጥሮ አደጋዎች ጋር ተያይዞ የሚመጡ ጉዳቶችን ለመቀነስ የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት የቅድመ ማስጠንቀቂያ ሥርዓቱን አጠናክሯል።

ይህም አደጋዎችን አስቀድሞ በመተንበይ፣ ፈጣን ጣልቃገብነት የሚያስፈልጋቸውን አካባቢዎች ለመለየትና ወቅታዊ እርምጃዎችን ለመውሰድ ያስችላል። እንዲህ ያሉ አስተማማኝና ሳይንሳዊ መረጃዎች ወደ ተግባራዊ መመሪያዎች ሲቀየሩ የዜጎችን ሕይወት ለማዳን፣ ሀብትና ንብረትን ለመጠበቅ እንዲሁም የተሻለ ብሔራዊ ውሳኔ ለመስጠት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታሉ።

በተጨማሪም ሀገራዊ ሉዓላዊነትንና ድንበርን ለማስከበር የኢትዮጵያን ታላቅነትና የወቅቱን ዓለም አቀፍ ሁኔታ ያገናዘበ ዘመኑን የዋጀ የመከላከያ ኃይል የመገንባት ሥራ እየተከናወነ ይገኛል።

 

በተለይም ዘመናዊ የድሮን ቴክኖሎጂዎችን በመታጠቅና የአየር ኃይሉን በዘመናዊ መሣሪያዎችና በሥልጠና በማበልጸግ፣ በምስራቅ አፍሪካ ቀጣና ሙሉ የአየር የበላይነትንና አስተማማኝ የደህንነት ከለላ ለመፍጠር የሚያስችል ወታደራዊና ቴክኖሎጂያዊ አቅም የመገንባት ሥራዎች በትኩረት እየተተገበሩ ይገኛሉ።

#የመደመርመንግሥት

በልዩ እሸቱ

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: