ባሕር ዳር የከተማ ውበትን ከዘመናዊ የመንግሥት ተቋማት ግንባታ ጋር በማቀናጀት የኢትዮጵያን አዲስ ገጽታ እያንጸባረቀች እንደምትገኝ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በከተማዋ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጽሕፈት ቤትና ቤተ መንግሥት ግንባታ ዛሬ በይፋ አስጀምረዋል።
ጣና ሐይቅና ዓባይ በሚታዩበት የጣና ማዕዘን ላይ የሚገነቡት እነዚህ ተቋማት፣ የክልሉን እሴቶችና መለያ ባህሪያት በሚያንጸባርቅ መልኩ በኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች የተነደፉ እንዲሁም ዘመናዊነትን ከሀገር በቀል እሳቤ ጋር ያጣመሩ ናቸው ብለዋል።
የግንባታዎቹ ቦታ መረጣና ዲዛይን በተሻለ መልኩ እንዲዘጋጁ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሙያዊ ሐሳብ ማበርከታቸውን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ አብራርተዋል።
ፕሮጀክቱ የመደመር መንግሥት የሥራ ከባቢን የማሻሻል፣ ዘመናዊና ጠንካራ ተቋማትን የመገንባት እንዲሁም ለሕዝብ የተሻለ አገልግሎት የመስጠት ራዕይ አካል እንደሆነም ጠቅሰዋል።
በተጨማሪም የመንግሥት ተቋማትን በዘመናዊ መልኩ ማደራጀት የከተማ ውበትን ከማሳደግ ባለፈ፣ የተሻለ አስተዳደርንና ውጤታማ የሕዝብ አገልግሎትን ለማረጋገጥ ወሳኝ ሚና እንዳለው አስገንዝበዋል።
#የመደመርመንግሥት #ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: