Search

“አዲስ አበባን የስፖርት ቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ የመላው ከተማዋ ነዋሪዎች ተሳትፎ ወሳኝ ነው”፦ ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ቅዳሜ ጥቅምት 07, 2019 46

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ 16ኛው የአዲስ አበባ ስፖርት ምክር ቤት ጉባኤ መካሄድ መጀመሩን ገልጸዋል።

ስፖርት ለጤንነት፣ ለአንድነት፣ ለወዳጅነት እንዲሁም ለከተማዋ የቱሪዝም እና የኢኮኖሚ ዕድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለውም ጠቁመዋል።

ከንቲባዋ አዲስ አበባን የስፖርት ቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ የመላው ከተማዋ ነዋሪዎች ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን ጠቁመው፤ ወጣቶችን፣ ሴቶችን፣ አካል ጉዳተኞችን እና ሁሉንም የማኅበረሰብ ክፍሎች በእኩልነት የሚያሳትፉ አሠራሮች ሊጠናከሩ እንደሚገባ አጽንዖት ሰጥተዋል።

ተደራሽና ጥራት ያላቸውን የስፖርት መሠረተ ልማቶች ማስፋፋት፣ መንከባከብ እና በኃላፊነት መጠቀም እንደሚያስፈልግ በመግለጽ፣ የስፖርት ዕድገት የሁሉም የጋራ ኃላፊነት መሆኑን እና በስፖርት በመሳተፍ፣ ወጣቶችን በመደገፍ እንዲሁም መሠረተ ልማቶችን በመጠበቅ የተሻለች አዲስ አበባን መገንባት እንደሚገባ ጥሪ አቅርበዋል።

#የመደመርመንግሥት

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: