የሲዳማ ክልል ምክር ቤት 7ኛ ዙር 1ኛ የስራ ዘመን የመጀመሪያ አስችኳይ ጉባኤውን በሀዋሳ ከተማ እያካሄደ ነው።
በምክር ቤቱ የክልሉን የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ያቀረቡት ርዕሰ መስተዳድር መሳይ ሀይሉ (ዶ/ር) በክልሉ የህዝብ ጥያቄ ሆነው የቆዩ የልማት ስራዎችን በመለየት ፈጣን ምላሽ እየሰጠን እንቀጥላለን ብለዋል።
በክልሉ አርሶአደሩን በግብዓት እና በቴክኖሎጂ በመደገፍ የግብርና ምርታማነትን ለማሳደግ የሚሰራ ሲሆን ለኢንዱስትሪ ግብዓት ለሚሆኑ የግብርና ምርቶች ልዩ ትኩረት ይሰጣል ብለዋል።
በእንስሳት ሀብት ልማት የዝርያ ማሻሻል፣ የእንስሳት ጤናና የመኖ አቅርቦትን በማሳደግ የቤተሰብ ብልጽግናን ለማረጋገጥ እንደሚሰራ አንስተዋል።
በተለያዩ ዘርፎች ለወጣቶች የሥራ ዕድል ለመፍጠር የክህሎት ሥልጠና የመስጠት እንዲሁም የብድር፣ የመሥሪያና የመሸጫ ቦታ አቅርቦትን ለማሟላት እንደሚሠራም አብራርተዋል።
በክልሉ የውሃ፣ የመንገድ ፣ የጤና እና የትምህርትና ተደራሽነትን እና ጥራትን በፍትሃዊነት ለማቅረብ ይሰራልም ብለዋል።
በተቋማት ያለውን የአገልግሎት አሰጣጥ በማዘመን ብልሹ አሰራሮችን ለማስቀረት ትኩረት እንደሚደረግም ርዕሰ መስተዳድሩ አንስተዋል።
ምክር ቤቱ በአስቸኳይ ጉባኤው የክልሉን የ2019 በጀት፣ የክልሉ የኦዲት እና ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዕቅድ እንደሚፀድቅ ይጠበቃል።
በአስረሳው ወገሼ
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: