Search

በ2019 የምርት ዘመን በመስኖ ከ185 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ስንዴ ለማምረት ግብ ተጥሎ እየተሠራ ይገኛል፦ ግብርና ሚኒስቴር

ሰኞ ጥቅምት 09, 2019 55

የግብርና ሚኒስቴር ለክልል ግብርና ቢሮ ባለድርሻ አካላት ሀገራዊ የመስኖ ስንዴ ንቅናቄ መድረክ ያዘጋጀ ሲሆን፣ በእርሻና ሆርቲካልቸር ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አማካሪ አሊ መሐመድ (ፕ/ር) የ2018 በጀት ዓመት የአፈጻጸም ሪፖርትና የ2019 ዕቅድ ውይይት ተደርጎበታል።

በመድረኩ በተገለጸው መረጃ መሠረት በ2018 በጀት ዓመት በመስኖ ከለማው ከ3 ነጥብ 7 ሚሊዮን ሄክታር በላይ መሬት ከ148 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ማግኘት ተችሏል።

መንግሥት ለዘርፉ የሰጠው ልዩ ትኩረት የኩታገጠም እርሻ መስፋፋት፣ የማዳበሪያ ግዥ ሥርዓት መሻሻል እንዲሁም ስትራቴጂካዊ እርምጃዎችንና ውጤትን መሠረት አድርጎ ማቀድና መፈጸም ካለፈው ዓመት የተገኙ ታላላቅ ተሞክሮዎች መሆናቸው ተመላክቷል።

በተያዘው የ2019 የምርት ዘመንም በ4 ነጥብ 5 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ላይ ከ185 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ስንዴ ለማምረት ግብ ተጥሎ ርብርብ እየተደረገ ይገኛል።

በመድረኩ  የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ሶፊያ ካሳ (ዶ/ር) በ2019 የምርት ዘመን የተጣለውን አገራዊ ግብ ለማሳካት በቂ የማዳበሪያ አቅርቦት የተዘጋጀ መሆኑን ገልጸው ሁሉም ባለድርሻ አካላት የተቀናጀ ርብርብ እንዲያደርጉ አሳስበዋል።

በመስኖ ስንዴ ልማቱ የመሬት ዝግጅት፣ የግብዓት አቅርቦት፣ የተባይና በሽታ ቁጥጥር እንዲሁም የመረጃ ልውውጥ ትኩረት የሚሹ ዋና ዋና ጉዳዮች መሆናቸው ተጠቅሷል።

ይህ በምግብ ራስን ለመቻልና በስንዴ ምርት የሚታየው ታሪካዊ እመርታ ኢትዮጵያ በፅኑ መሠረት ላይ የተገነባች #ትልቅሀገር፣ በስራና በምርት የላቀ ቁርጠኝነት የሚያሳይ #ትልቅሕዝብ እና ለወደፊቱ የተዘረጋ #ታላቅርዕይ ያላት ሀገር መሆኗን በተግባር ያረጋገጠ ነው።

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: