Search

ሕዳሴ ከሁሉም ማዕዘናት ወደ አንድ ሀገራዊ የልማት ዕሳቤ እየተደመሩ ኃያል የመሆን እና የመተባበር ህያው ምልክት ነው- ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

ማክሰኞ መስከረም 06, 2018 53

ሕዳሴ ከሁሉም ማዕዘናት ወደ አንድ ሀገራዊ የልማት ዕሳቤ እየተደመሩ ኃያል የመሆን እና የመተባበር ህያው ምልክት ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ገልጸዋል፡፡
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስተሩ በማህበራዊ የትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ ዛሬ በአማራ ክልል በተለያዩ ከተሞች ሕዝቡ ያሳየው ታላቅ የድጋፍ ሰልፍ ገጸ ብዙ ትርጉም ያለው ሰልፍ ነው ብለዋል።
በዚህም የክልሉ ሕዝብ ቃሉም ተግባሩም ለልማት የወገነ መሆኑን አሳይቷል ነው ያሉት፡፡
በአማራ ክልል የተስተዋለው የዛሬው ሰልፍ እንደዓባይ ለታላቅ ግብ የመደመር፣ ፈተናዎችን እያሸነፉ መሻገር፣ ለልማት የተከፈለን መስዋዕትነት የማክበር የከበረ የሕዝብ ድምጽ መሆኑን አመልክተዋል።
እንደዚህ ያሉ የሕዝብ ታላላቅ ሰልፎች ለቀጣይ የኢትዮጵያ ግዙፍ ልማቶች የሚያተጋን የብርታት ደወል ነው ሲሊም ገልጸዋል።