Search

ኢራን ከአሜሪካ ጋር የገባሁት ስምምነት አልተከበረም በሚል የሆርሙዝ ሰርጥን መልሳ መዝጋቷን አስታወቀች

ቅዳሜ ሰኔ 13, 2018 54

የኢራን ማዕከላዊ ወታደራዊ ዕዝ እስራኤል በደቡባዊ ሊባኖስ የምትፈጽመው ጥቃት ከአሜሪካ ጋር የተደረሰውን ስምምነት የሚጥስ በመሆኑ የሆርሙዝ ሰርጥን መዝጋቱን አስታውቋል።

የኢራን አብዮታዊ ዘብ ባሕር ኃይል የባሕር መተላለፊው ለሁሉም መርከቦች በመዘጋቱ ማናቸውም መርከቦች የወደ ሰርጡ የሚቀርቡ ከሆነ ለአደጋ ስለሚጋለጡ መርከባቸውን ከሆርሙዝ እንዲያርቁ አስጠንቅቋል።

May be an image of map

አብዮታዊ ዘቡ  በአገሪቱ ቴሌቪዥን በቀረበው መግለጫ ላይ አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት መድረሳቸውን ተከትሎ አርብ ዕለት ሙሉ ለሙሉ የተከፈተው ወሳኙ የባሕር ላይ መተላለፊያ ለሁሉም መርከቦች ዝግ እንደሚሆን አሳውቋል።

ኢራን ከአሜሪካ ጋር በደረሰችው የመግባቢያ ስምምነት ላይ እስራኤል በሊባኖስ ላይ የምታካሂደው ተከታታይ ጥቃት እንደሚቆም የተገለጸ ቢሆንም ግጭቱ በመቀጠሉ ኢራን ስምምነቱ ተጥሷል ማለቷን የቢቢሲ እና አልጀዚራ ዘገባ ያመለክታል።