ሀገራችን ኢትዮጵያ በከተሞች ገጽታ ግንባታና በታላላቅ የመሠረተ-ልማት ዝርጋታዎች ረገድ ታሪክ የማይረሳው ታላቅ እመርታ ላይ ትገኛለች።
በተለይም በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጀመሩት የገበታ ፕሮጀክቶች እና ከተሞችን እያደሱና እያስዋቡ የሚገኙት የኮሪደር ልማት ሥራዎች የከተሞቻችንን ይዘት ሙሉ በሙሉ በመለወጥ ላይ ናቸው።
ከዚህ የተቀናጀ ልማት ጎን ለጎን የቱሪዝም እና የኢኮኖሚ ትስስር ይበልጥ ለማሳደግ የ7 አዳዲስ ኤርፖርቶች ግንባታ የኢትዮጵያን የነገ ብልጽግና በጽኑ መሠረት ላይ እየገነቡ መሆናቸውን ያረጋግጣሉ።
ይህ የተቀናጀና ሁሉን አቀፍ የከተሞች መለወጥ ጉዞ የሀገራችንን የእድገት ምዕራፍ ወደ አዲስ ከፍታ እያሸጋገረው ይገኛል!