Search

የአፍሪካ ህብረት በኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ግስጋሴ ላይ ሙሉ እምነት አለው!፦ አምባሳደር ባንኮሌ አዶዬ

ሰኞ ሰኔ 15, 2018 71

የአፍሪካ ህብረት ታዛቢ ልዑክ እና የህብረቱ የፖለቲካ ጉዳዮች፣ የሰላምና ደህንነት ኮሚሽነር አምባሳደር ባንኮሌ አዶዬ በትላንትናው እለት የምርጫ ውጤት ይፋ በተደረገበት መርኃ-ግብር ላይ ባደረጉት ንግግር የዚህ ዴሞክራሲያዊ ሽግግር ስኬት የሴቶችን እና የወጣቶችን አካታች ተሳትፎ፣ እንዲሁም የኢትዮጵያን ነፃ ፍላጎት መሰረት ያደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

የአፍሪካ ህብረት የዴሞክራሲ ተቋማትን ለማጠናከር ያለውን ቁርጠኝነት ያረጋገጡት ተወካዩ፣ አፍሪካ ዴሞክራሲን ከመቀበል ውጭ ሌላ ምርጫ እንደሌላት እና ይህም ልማትን፣ ሰላምን እና ዘላቂነትን ለማምጣት የተሻለው መንገድ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል።

አምባሳደር ባንኮሌ አዶዬ ኢትዮጵያ ወደ ሰላም፣ መረጋጋት እና ዴሞክራሲያዊ አስተዳደር ለምታደርገው ቀጣይነት ያለው ግስጋሴ ሕብረቱ ሙሉ እምነት እንዳለው አስታውቀዋል።