Search

የአንድ ዶሮ ዕድሜ ምን ያህል ነው?

ሓሙስ ሚያዝያ 08, 2018 71

በአሜሪካ የተገኘችው ዶሮ 15 ዓመት ከ100 ቀናት ዕድሜ ላይ መገኘቷ በዓለም ላይ በሕይወት ያለች በዕድሜ ትልቋ ዶሮ አስብሏታል።

እንዲህ ያሉትን ያልተለመዱ እና አስደናቂ ጉዳዮችን የሚመዘግበው የዓለም ድንቃድንቆች መዝገብም ይህችን ዶሮ በመዝገቡ ላይ አስፍሯታል።

‘ጌርቲ’ በሚል መጠሪያ የምትታወቀው ይህች ዶሮ በአሜሪካ፣ ቴክሳስ የምትኖረው እና ‘ፐርል’ በሚል መጠሪያ የምትታወቀው ዶሮ ከዚህ ቀደም ይዛው የቆየችውን ክብረ ወሰን በ6 ወራት ማሻሻሏ ተገልጿል።

ባለፉት 15 ዓመታት አራት የዶሮ ትውልዶች ሲያልፉ፣ በቡናማና ጥቁር ነጠብጣብ ላባዎች የደመቀችው ‘ጌርቲ’ ግን ረጅም እድሜ በሕይወት መቆየት የቻለች ብቸኛዋ ዶሮ ሆናለች።

‘ጌርቲ’ አሁን ላይ እንቁላል መጣል ማቆሟን እንዲሁም ዓይኖቿ መታወራቸው በሌሎች ዶሮዎች እንድትጠቃ እንዳደረጋት የዶሮዋ ባለንብረት ፍራንክ ቱሬክ ተናግሯል።

በሀና ምንዳሁን

#GuinnessWorldRecords #oldestchicken #USA #EBC

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ:

ተያያዥ ዜናዎች: