Search

የ4ኛው የጂ-ፓወር ቲክቶክ ክሬቲቭ አዋርድ እየተካሄደ ነው

ቅዳሜ ኅዳር 19, 2019 611

ለ3 ወራት ሲካሄድ የቆየውን የድምፅ አሰጣጥ ሂደት ያጠናቀቀው 4ኛው የጂ-ፓወር ቲክቶክ ክሬቲቭ አዋርድ የፍጻሜ ሥነ ሥርዓት ተጀምሯል።

በመድረኩ ከተወዳዳሪዎች በተጨማሪ በርካታ የማኅበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች፣ ታዋቂ የይዘት ፈጣሪዎች፣ የጥበብ ባለሙያዎች እንዲሁም የተለያዩ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

ከ25 በላይ በሚሆኑ የተለያዩ ዘርፎች እጩዎችን ያካተተው ይህ ውድድር፣ ዘንድሮ ከፍ ያለ አጠቃላይ የገንዘብ ሽልማት ያዘጋጀ ሲሆን፤ ለዋናው አሸናፊም ከአምናው የመኪና ሽልማት በላቀ መልኩ ዘመናዊ መኖሪያ ቤት ይበረከትለታል።

የሽልማት ሥነ-ሥርዓቱን የመርኃ ግብሩ ብቸኛ የሚዲያ አጋር በሆነው በኢቢሲ የመዝናኛ ቻናል፣ በኢትዮሳት ፍሪኩዌንሲ 11165 ፖላራይዜሽን Horizontal (H) ሲምቦል ሬት 45000 እንዲሁም በዲኤስቲቪ (DStv) ቻናል 473 በቀጥታ ስርጭት ይከታተሉ።

በሃና ምንዳሁን

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: