Search

በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ የታገዘ የተቀናጀ የሚዲያ ሬጉላቶሪ እና አስተዳደር ስርዓት ተመረቀ

ዓርብ ሚያዝያ 23, 2018 61

ዛሬ የተመረቀው የሚዲያ ሬጉላቶሪ እና አስተዳደር ስርዓት የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ከኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ጋር በትብብር የለማ ነው።
የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) ሚዲያ ለብሔራዊ ጥቅም ያለውን ሚና ለማሳደግ በቴክኖሎጂ የተደገፈ ስርዓት መዘርጋት ከፍተኛ ሚና እንዳለው አመልክተዋል ።
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሀይማኖት ዘለቀ እንደገለፁት ስርዓቱ በኢትዮጵያ ፈቃድ ወስደው የሚሰሩ መገናኛ ብዙሃንን በዘመናዊ የሚዲያ ቁጥጥርና ስርዓት ፕሮፋይላቸውን ዲጂታላይዝ ለማድረግና የይዘት ቁጥጥሩን በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ የታገዘ የሚያደርግ ነው።
ይህም ዘመናዊ የሚዲያ ስርዓትን ውጤታማ በማድረግ የጥላቻ ንግግርና የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመቀነስ እንዲሁም የዜጎችን ተሳትፎ በማሳደግ አስተዋጽኦ አለው።
የቴክኖሎጂ ስርዓቱ ዜጎች ካሉበት ቦታ ሆነው ጥቆማ ማቅረብና መከታተል እንዲችሉ፣ የተደራጀ የጥቆማና ቅሬታ መረጃ እንዲኖር ፣ የተቀናጀ የሚዲያና ጋዜጠኞች መረጃ እንዲኖር እንዲሁም መረጃ ላይ የተመሰረተ ውሳኔ ለመስጠት ያግዛል ተብሏል።
በሞላ ዓለማየሁ