አሜሪካ እና ኢራን በተፈራረሙት ባለ 14 ነጥብ የመግባቢያ ስምምነት ውስጥ የዓለም የነዳጅ ንግድ መተላለፊያ የሆነው የሆርሙዝ ሰርጥን ክፍት ማድረግ ይገኝበታል።
ስምምነቱን ተከትሎ አሜሪካ በኢራን ላይ የጣለችውን እገዳ በማንሳቷ ከቻባሃር በስተምዕራብ ታግተው የነበሩ 72 ሚሊዮን በርሜል ነዳጅ የጫኑ መርከቦች የጫኑትን ነዳጅ ለገበያ ለማቅርብ ይተማሉ።

በጦርነትና በማዕቀብ ታንቆ ለቆየው የዓለም ኢኮኖሚ ከፍተኛ የአቅርቦት መጠን በማሳደግ የነዳጅ ዋጋ መናርን ለመቀነስ ትልቅ መፍትሄ ይሆናል ተብሏል።
ግጭቱን ተክትሎ ተዘግቶ የቆየው የሆርሙዝ ሰርጥ መከፈት፣ በባህረ ሰላጤው ውስጥ ታግተው የነበሩ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ በርሜል ድፍድፍ ነዳጆችን የጫኑ መርከቦች በአንድ ጊዜ ወደ ዓለም ገበያ የሚያስገባ በመሆኑ የነዳጅ ዋጋን በከፍተኛ ሁኔታ ያረጋጋዋል ተብሎ ይጠበቃል።
በፋርስ ባህረ ሰላጤ ውስጥ ተዘግቶ የቆየ 93 ሚሊዮን በርሜል ድፍድፍ ነዳጅ በነፃነት እንዲያልፍ ይለቀቃል ሲል ሮይተርስ ባወጠው ዘገባ አመለክቷል። በባህረ ሰላጤው ውስጥ 87 ሚሊዮን በርሜል የሚገመት ነዳጅ ጭነው ቆመው የነበሩ 54 ግዙፍ የነዳጅ መርከቦችም ጉዟቸውን ይጀምራሉ ተብሏል።
ቀደም ሲል የዓለምን አንድ አምስተኛ የነዳጅ ጭነት ያስተላልፍ የነበረው ይህ ወሽመጥ፣ አሁን ላይ የኢራን መርከቦችም ጭምር መንቀሳቀስ በመጀመራቸው የቀጠናውን የንግድ የበላይነት መልሶ ያረጋግጣል።