Search

የጠቅላይ ሚኒስትሩ እንግዶች ምን ገጠማቸው?

ቅዳሜ ሰኔ 13, 2018 50

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ያጋሩት የቴክኖሎጂንና የፖሊስን ቅንጅት የሚያሳይ አስገራሚ ታሪክ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአፍሪካ ቀዳሚ የሆነውን የተቀናጀ የዲጂታል አገልግሎት መተግበሪያ መርቀው ሥራ ሲያስጀምሩ ባደረጉት ንግግር የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ከቦሌ እስከ ዋናው መሥሪያ ቤት የCCTV ካሜራ ተጠቅሞ ወንጀለኞችን እንዴት ተከታትሎ በቁጥጥር ስር እንዳዋለ አንድ አስገራሚ ታሪክ አጋርተዋል።

May be an image of television, speaker, newsroom and text

ከትናንት በስቲያ የተፈጠረ አጋጣሚ ነው። የጠቅላይ ሚኒስትሩ እንግዶች አዲስ አበባ መጡ። ለሥራ የመጡ የውጭ ዜጎች ናቸው። ኢትዮጵያን ሲያዩ የመጀመሪያቸው ነበር።

ቀን ላይ ከተማዋን ተዘዋወሩ ጎበኙ። የሪቨርሳይድ ከተማ ኮሪደርም የጉብኝቱ አካል ነበር። በሀገራችን ውበት እጅግ ተማረኩ። "እንዴት የምታምር ሀገር ናት!" በማለት አደነቁ።

ምሽት ላይ አየር ለመቀበል ከሀያት ሆቴል ወጥተው በእግራቸው መንቀሳቀስ ጀመሩ። በዚህ መሀል ያልታሰበ ነገር ተፈጠረ። ሁለት ሦስት ሰዎች ድንገት ወደ እነሱ በመጠጋት የእንግዶቹን ሞባይል ነጥቀው ተሰወሩ። ሰዓቱ ማታ 4 ሰዓት ገደማ ነበር።

ቀኑን ሙሉ ሲያደንቁ የዋሉት እንግዶች አዘኑ። ማታ 4 ሰዓት ከ10 ላይ ለአዲስ አበባ ፖሊስ ስልክ ተደዎሎ የተፈተረው ነገር ተነገራቸው።

ከዚያ በኋላ የሆነው ግን ተዓምር ነበር። አምስት ሰዓታት ብቻ አለፉ። ሌሊት 9 ሰዓት ላይ የአዲስ አበባ ፖሊስ የእንግዶቹን በር አንኳኳ። የተሰረቀውን ሞባይል ይዘው ከተፍ አሉ።

እንግዶቹ ማመን አቃታቸው። "የመንገዱን ንጽሕና፣ ኮሪደሩንና ዛፉን ስናደንቅ ውለናል" አሉ። "ይህን ተዓምር ግን ፈጽሞ አልጠበቅንም!" በማለት ተገረሙ።

አክለውም፣ "ገንዘብ ተደራድረን ከፍለን እንኳን እቃችንን እናገኛለን ብለን አላሰብንም። ፖሊስ በነፃ በራችንን አንኳኩቶ ያመጣል ብለን አልገመትንም" በማለት ታላቅ ደስታቸውን ገለጹ።

ይህንን የሰሙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደኋላ መለስ ብለው ታሪኩን በማስታወስ፤ "ያኔ ካሜራ ለመትከል መሟገታችንና ተለምኖም ቢሆን መሠራቱ እንኳን ሆነ፤ እነሆ ዛሬ ያደረግነው ጥረት ፍሬ አፍርቶ መልሶ ከፈለን" በማለት ስሜታቸውን ገልጸዋል።

May be an image of television, newsroom and text

ጊዜው ከ20 ዓመት በፊት ነበር። ከቦሌ እስከ ፌዴራል ፖሊስ ዋና መሥሪያ ቤት የደህንነት ካሜራ እንዲዘረጋ ጥያቄ ቀረበ። ፌዴራል ፖሊስ ክፍያ መክፈል አልችልም አለ። ሆኖም ፕሮጀክቱ በነፃ እንዲሠራ ተወሰነ። ይህንን ለማሳካት ለወራት የፈጀ ፍትግያ ነበረ። ድካሙ ግን ከንቱ አልነበረም።