Search

የሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ለብልጽግና ፓርቲ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ

ማክሰኞ ሰኔ 16, 2018 72

የሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ "በኢትዮጵያ የፓርላማ ምርጫ ላስመዘገቡት ድል፣ ለወዳጄ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (/) እና ለብልጽግና ፓርቲ ከልብ የመነጨ የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክቴን አስተላልፋለሁ ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሕንድ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ታሪካዊ፣ ሁለገብ እና ሥር የሰደደ ግንኙነት ከፍ አድርጋ ትመለከታለች ብለዋል በማኅበራዊ መልዕክታቸው።

ባለፈው ዓመት በኢትዮጵያ ያደረጉትን ጉብኝት በጥሩ ትዝታ እንደሚያስታውሱ ገልጸው፣ ስትራቴጂያዊ አጋርነታችንን እና በሕዝቦቻችን መካከል ያለውን የወዳጅነት ትሥሥር ይበልጥ ለማጠናከር በቅርበት በጋራ ለመሥራት በጉጉት እጠብቃለሁ ብለዋል።