Search

የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን የ7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ስኬታማነት አደነቀ

ማክሰኞ ሰኔ 16, 2018 58

የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ማህሙድ አሊ ዩሱፍ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት እና ሕዝብ 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ በተሳካ ሁኔታ በማካሄዳቸው አድናቆታቸውን ገልጸዋል።

ሊቀመንበሩ ባወጡት መግለጫ የምርጫው ሂደት ኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲን የማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ልማት መሰረት አድርገው ለማጠናከር ያላቸውን ቁርጠኝነት ያሳየ መሆኑን ጠቅሰዋል።

በተጨማሪም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አጠቃላይ ምርጫው በተሳለጠ መንገድ እንዲካሄድ ያሳየውን ሙያዊ ብቃት እና ቁርጠኝነት አድንቀዋል።

ሊቀመንበሩ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ይፋ ባደረገው ውጤት መሰረት በአብላጫ ድምፅ ድል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (/) እና ለብልጽግና ፓርቲ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በመጨረሻም የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን በአባል ሀገራት ውስጥ ተአማኒ፣ ሰላማዊ እና ግልጽ በሆነ የምርጫ ሂደት ዴሞክራሲያዊ አስተዳደርን ለማጠናከር ያለውን ጽኑ አቋም በድጋሚ አረጋግጠዋል።