የጎቤ እና ሽኖዬ ፌስቲቫልን ወጣቶች በባህላዊ አልባሳት ደምቀው በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ላይ እያከበሩት ይገኛሉ።
“ጎቤና ሽኖዬ'' ወጣት ወንዶች እና ሴቶች ክረምቱ አልፎ የ'ብራ' ወቅት መምጣቱን ለማመላከት በባህላዊ አልባሳት አጊጠው የሚጨፍሩት ባህላዊ ጭፈራ ነው።
በዓሉ ወጣት ወንዶችና ሴቶች የተለያዩ ባህላዊ አልባሳት አጊጠው ትውፊቱን በጠበቀ መንገድ የሚያከብሩት ሲሆን፣ ፌስቲቫሉ ወጣቶች አንድነታቸውን ያጠናከሩበት፣ ደስታቸውን ያጋሩበትና ተስፋቸውን ያንጸባረቁበት ነው።
ወጣቶቹ በተለያዩ ጎዳናዎች ለታዋቂ ግለሰቦች፣ ለመንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እና መኖሪያ ቤቶች እየተዘዋወሩ የእንኳን አደረሳችሁ መልካም ምኞት በመግለጽ የተለያዩ ስጦታዎችን የሚቀበሉነት በዓል ነው፡፡
በሃይማኖት ከበደ
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: