Search

ከቢሊዮን ወደ ትሪሊዮን የኢትዮጵያ የገቢ አሰባሰብ ታሪካዊ እመርታ በጳጉሜን 1 የእመርታ ቀን ሲቃኝ

እሑድ ጳጉሜን 01, 2018 21

ሀገራችን ኢትዮጵያ 13ኛዋ ወር ጳጉሜን የመጀመሪያ ቀን በሆነው የእመርታ ቀን የሁለንተናዊ እድገቷን ፍሬዎች እና የተመዘገቡ ታሪካዊ ስኬቶችን በጋራ ታከብራለች።

ከእነዚህም የልማት እና የብልጽግና ስኬቶች መካከል በለውጥ ዓመታት የታየው የግብር አሰባሰብ ሥርዓት ከቢሊዮን ወደ ትሪሊዮን ብር ማደግ የሀገራችንን የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትና የፋይናንስ ነፃነት ማረጋገጫ ታላቅ እመርታ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (/) 2018 በጀት ዓመት ሪፖርት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረቡበት ወቅት እንደገለጹት፣ ኢትዮጵያ ባለፉት 27 ዓመታት በአጠቃላይ የሰበሰበችው ገቢ 1 ትሪሊዮን ብር እንኳን የማይሞላ የነበረ ቢሆንም፣ 2018 በጀት ዓመት ብቻ ግን 1.5 ትሪሊዮን ብር ገቢ በመሰብሰብ 150% በላይ ታሪካዊ ብልጫ ያለው እመርታ ማስመዝገብ ተችሏል።

ይህ በምርት ቀን የምናከብረው ታሪካዊ ሽግግር የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን በማስፋፋት፣ የግብር ህጎችን በማሻሻል እና የታክስ መሠረቱን በማስፋት የተገኘ ታላቅ ውጤት ነው።

ግብር ከፋዮች በአካል ሳይገኙ በይነመረብን በመጠቀም ግብራቸውን የሚያስታውቁበትና የሚከፍሉበት የዲጂታል ታክስ ሥርዓት በመዘርጋቱ የታክስ ስወራን እና የቢሮክራሲ እንግልትን በእጅጉ መቀነስ ተችሏል።

በተጨማሪም አዳዲስ የንግድ ዘርፎችን ወደ ግብር ሥርዓቱ በማስገባትና ግብር መክፈል የሀገር ፍቅር መገለጫ ነው የሚል ባህል እንዲዳብር በማድረግ ሰፊ የገቢ መሠረት ተጥሏል።

የግብር ገቢ ከቢሊዮን ወደ ትሪሊዮን ማደጉ እንደ የኮሪደር ልማት፣ የትምህርትና ጤና መሰረተ ልማቶች እንዲሁም የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታን የመሳሰሉ ግዙፍ ሀገራዊ ፕሮጀክቶችን በራስ አቅም ለመሸፈን የሚያስችል አቅም በመፍጠሩ የጳጉሜን 1 የእመርታ ቀን አዲሱን የኢትዮጵያ የብልጽግና ምዕራፍ በግልጽ ያበስራል።

 

በአድማሱ አራጋው

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: