Search

ኢትዮጵያ እና ሕንድ ስትራቴጂያዊ አጋርነታቸውን እና ትብብራቸውን ይበልጥ ለማሳደግ ተስማሙ

ዓርብ መስከረም 29, 2019 52

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የሕንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር  ዶ/ር ሱብራህማንያም ጃይሻንካር እና የልዑካን ቡድናቸውን ተቀብለው አወያይተዋል።

በውይይቱ ወቅት በኢትዮጵያ እና በሕንድ መካከል ያለው ጠንካራ እና የቆየ ወዳጅነት በድጋሚ የተረጋገጠ ሲሆን፤ ሁለቱ ሀገራት ያላቸውን ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር በሚችሉበት ሁኔታ ላይ መክረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሰሞኑ በሕንድ ያደረጉትን ጉብኝት እና ከጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ጋር የነበራቸውን ስኬታማ ቆይታ ተከትሎ፣ የሁለቱን ሀገራት ወዳጅነት በተጠናከረ ትብብርና በስትራቴጂካዊ አጋርነት ላይ ተመስርቶ ይበልጥ ማሳደግ በሚቻልባቸው ዕድሎች ላይ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጋር ውጤታማ ውይይት ማድረጋቸውን ገልጸዋል።

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: