Search

የCOP32 ተመራጭ ፕሬዚዳንት ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከጣልያን የአካባቢና የኢነርጂ ደኅንነት ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

ሓሙስ ኅዳር 10, 2019 113

የCOP32 ተመራጭ ፕሬዚዳንት ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከጣልያን የአካባቢና የኢነርጂ ደኅንነት ሚኒስትር ጊልቤርቶ ፒኬቶ ፍራቲን ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አካሂደዋል።

በውይይታቸውም በኢትዮጵያና በጣልያን መካከል ባለው ዘላቂ ወዳጅነትና ጠንካራ የሁለትዮሽ ግንኙነት ላይ በመመስረት፣ ለአየር ንብረት ርምጃ ያላቸውን የጋራ ቁርጠኝነት አረጋግጠው፣ ለተሳካ COP32 ዝግጅት ትብብራቸውን የበለጠ ለማጠናከር ተስማምተዋል።

የሰው ዘር መገኛ፣ የፅናት እና የተስፋ ምድር የሆነችው ኢትዮጵያ ዓለም አቀፉን አየር ንብረት ጉባኤ ለማስተናገድ የምታደርገውን ሀገራዊ እንቅስቃሴ በተመለከተ ሙሉ እና ትክክለኛ የጉባኤውን መረጃዎች ከምንጩ ለማግኘት ሁልጊዜም የኮፕ-32 ይፋዊ ድረ-ገጽ https://cop32ethiopia.et/ ይጠቀሙ።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: