ኢትዮጵያና ስዊድን በአየር ንብረት ለውጥ ዙሪያ ያላቸውን የሁለትዮሽ ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር በቱርክ አንታሊያ እየተካሄደ ከሚገኘው የCOP31 ጉባኤ ጎን ለጎን ውይይት አካሂደዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና የCOP32 ተመራጭ ፕሬዚዳንት ጌዲዎን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከስዊድን የአየር ንብረትና አካባቢ ሚኒስትር ሮሚና ፑርሞክታሪ ጋር ባደረጉት ምክክር፤ በአየር ንብረት እርምጃ፣ በፋይናንስ አቅርቦት፣ የአየር ንብረት ለውጥን በመቋቋም እንዲሁም በታዳሽ ኃይል ልማት ዘርፎች ያላቸውን አጋርነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር መክረዋል።
በውይይታቸውም ዘላቂ ልማትን ከማረጋገጥ ባለፈ የዓለምን የሙቀት መጨመር በ1.5 ዲግሪ ሴልሺየስ ወሰን ውስጥ ለመገደብ የተያዘውን ዓለም አቀፍ ግብ ለማሳካት የባለብዙ ወገን ትብብርና የማያቋርጥ ቁርጠኝነት ወሳኝ መሆኑን በጋራ አጽንኦት ሰጥተዋል።
በተጨማሪም ኢትዮጵያ ለምታስተናግደው የCOP32 ዓለም አቀፍ ጉባኤ ስኬታማነት የሚያግዙ የትብብር መስኮችን በመለየት ስዊድን የበኩሏን ድጋፍ እንድታበረክትና በጋራ እንዲሰሩ ሁለቱ ሚኒስትሮች ተስማምተዋል።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: