የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና ኮፕ 32 ተመራጭ ፕሬዚዳንት ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) በCOP31 እና COP32 ፕሬዚዳንትነት መካከል ያለውን ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር፣ ከCOP31 የድርድር ፕሬዚዳንት ክሪስ ቦወን ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አካሂደዋል።
ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) የCOP31 ፕሬዚዳንትነት በድርድሩ ያሳየውን አመራር በማድነቅ ግልጽና አካታች ሂደቱን፣ የመጀመሪያውን ውሳኔ (cover decision) ረቂቅ በቅድሚያ መለቀቁን እና እስካሁን የተመዘገበውን ውጤት አድንቀዋል።
ኢትዮጵያ ለተሳካ ውጤት ያላትን ድጋፍ በድጋሚ በማረጋገጥ፣ COP31 ለCOP32 መሰረት የሚሆን ጠንካራና ግልጽ ውጤት ይዞ እንዲጠናቀቅ ተስፋ እንዳላቸው ገልጸዋል።
የCOP31 የድርድር ፕሬዚዳንት ክሪስ ቦወን በበኩላቸው፣ ኢትዮጵያ ለኤሌክትሪፊኬሽን ትግበራ አጀንዳ ለሰጠችው ድጋፍ አመስግነው፣ ወደ ተጨባጭ ውጤቶች ለመቀየር ያላቸውን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል።
በተጨማሪም አውስትራሊያ ከኢትዮጵያ ጋር በመተባበር የተሳካ COP32 እንዲካሄድ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኗን አመላክተዋል።
የሰው ዘር መገኛ፣ የፅናት እና የተስፋ ምድር የሆነችው ኢትዮጵያ ዓለም አቀፉን አየር ንብረት ጉባኤ ለማስተናገድ የምታደርገውን ሀገራዊ እንቅስቃሴ በተመለከተ ሙሉ እና ትክክለኛ የጉባኤውን መረጃዎች ከምንጩ ለማግኘት ሁልጊዜም የኮፕ-32 ይፋዊ ድረ-ገጽ https://cop32ethiopia.et/ ይጠቀሙ።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: