Search

የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን በባንግኮክ ከአይኤምኤፍ (IMF) ከፍተኛ ኃላፊዎች ጋር ውይይት አደረገ

ማክሰኞ ጥቅምት 03, 2019 63

በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ የሚመራው ልዑካን ቡድን በባንግኮክ እየተካሄደ ከሚገኘው የ2026 የዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት (IMF) እና የዓለም ባንክ ቡድን (World Bank Group) ዓመታዊ ስብሰባ ጎን ለጎን የሁለትዮሽ ውይዮችን አካሂዷል።

በዚህም ከዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት (IMF) የፊስስካል ጉዳዮች መምሪያ እና ከገንዘብና ካፒታል ማርኬት መምሪያ ሃላፊዎች ጋር ፍሬያማ የሁለትዮሽ ውይይቶችን አካሂዷል።

ከፊስካል ጉዳዮች መምሪያ የሥራ ሃላፊዎች ጋር የተደረገው ውይይት በገንዘብ ሚኒስቴር (Ministry of Finance) የአቅም ግንባታ ላይ ያተኮረ ነው።

በዚህም እየተከናወኑ ያሉ የቴክኒክ ድጋፎችን መገምገም እና ከሚኒስቴሩ የሪፎርም ቅደም ተከተሎች ጋር የተጣጣሙ ተጨማሪ የድጋፍ ዕድሎችን መመርመር ላይ ትኩረት አድርጓል።

በሌላ በኩል ከገንዘብና ካፒታል ማርኬት መምሪያ ሃላፊዎች (Monetary and Capital Markets Department - MCM) ጋር የተካሄደው ስብሰባ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክን አቅም በመገንባት ላይ ያተኮረ ነበር።

በውይይቱም የዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት (IMF) እያደረገ ያለው የቴክኒክ ድጋፍና ተቋማዊ አቅምን ለማጠናከር እንዲሁም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክን የሪፎርም አጀንዳን ለማስቀጠል የሚያስችሉ ተጨማሪ የድጋፍ መስኮች ተዳስሰዋል።

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: