የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዢ እዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) በባንግኮክ እየተካሄደ ከሚገኘው የዓለም ባንክ እና የዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት (IMF) ዓመታዊ ስብሰባ ጎን ለጎን ከተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች ማዕከላዊ ባንክ ገዢ ካሊድ ሞሃመድ ባላማ ጋር ተወያይተዋል።
ገዢዎቹ በሁለቱ ሀገራት መካከል ባለው የፋይናንስ እና የባንክ ዘርፍ ያለውን ትብብር የበለጠ ማጠናከር በሚቻልበት እንዲሁም የልምድ ልውውጥ ማድረግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መክረዋል።
ውይይቱ በኢትዮጵያ እና በተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች መካከል ያለውን ጠንካራ የሁለትዮሽ ግንኙነት እና የቆየ አጋርነት ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግር መሆኑ ተገልጿል።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: