Search

ፈረንሳይ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ እንደምትደግፍ ገለጸች

ማክሰኞ ጥቅምት 03, 2019 48

በብሔራዊ ባንክ ገዢ እዮብ ተካለኝ (ዶ/ር) የተመራው የኢትዮጵያ ልዑክ በታይላንድ ባንኮክ እየተካሄደ በሚገኘው የ2026 የዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት (IMF) እና የዓለም ባንክ ቡድን ዓመታዊ ስብሰባ ጎን ለጎን ከፈረንሳይ የፋይናንስ ሚኒስትር ቶማስ ሪቪያል ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አድርጓል።

ውይይቱ በኢትዮጵያ እና በፈረንሳይ መካከል ያለውን የረጅም ጊዜ የኢኮኖሚ አጋርነት ለመገምገም ያስቻለ ነው።

ኢትዮጵያ እያካሄደች ባለው የሀገር በቀል የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ የተመዘገቡ ውጤቶችን ያደነቁት ሚኒስትሩ፤ ፈረንሳይ የኢትዮጵያን የልማት ሂደቶች ለመደገፍ የምታደርገውን ቀጣይነት ያለው አጋርነት አጠናክራ እንደምትቀጥል ገልጸዋል።

በተጨማሪም በልማት ፋይናንስ፣ በዕዳ ዘላቂነት፣ በኢንቨስትመንት እና በተቋማት አቅም ግንባታ ዘርፎች ትብብርን የበለጠ ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ሰፊ ምክክር ተደርጓል።

የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ መረጋጋት እና ዘላቂ ዕድገት ለማረጋገጥ የሁለቱ ሀገራት አጋርነት መቀጠል አስፈላጊ መሆኑ ተጎልቶ ተገልጿል።

#የመደመርመንግሥት

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: