የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አህመድ ሽዴ በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ከሆኑት ችን ሃይ ጋር የሁለትዮሽ ግንኙነትን በሚያጠናክሩ አጀንዳዎች ዙሪያ ተወያይተዋል።
ውይይቱ በሁለቱ ሀገራት መካከል በተለያዩ መስኮች የቆየውን የሁለትዮሽ ትብብር ማጠናከርና በፓርላማዎቻቸው መካከል ያለውን ግንኙነት ማጎልበት ላይ ያተኮረ ነው።
አምባሳደር ችን ሃይ በዚሁ ወቅት፣ አቶ አህመድ ሽዴ በአፈ ጉባኤነት በመሰየማቸው “እንኳን ደስ አለዎት” በማለት፣ የሥራ ዘመናቸው የተሳካ እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: