Search

“ግብፅ ኢትዮጵያ የባሕር በር እንዳታገኝ እና በወንዞቿ እንዳትጠቀም ለዘመናት ስትሠራ ቆይታለች”፡- አቶ ጁነይዲን ሳዶ

ረቡዕ ጥቅምት 04, 2019 101

ግብፅ ኢትዮጵያ የባሕር በር እንዳታገኝ የውኃ ሀብቷን በነፃነት እንዳትጠቀም ከ100 ዓመታት በላይ ተጽዕኖ ስታደርግ መቆየቷን የቀድሞው የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ፕሬዚዳንት አቶ ጁነይዲን ሳዶ ተናገሩ።

ኢትዮጵያ በኢኮኖሚ ከጎለበተች እና የጸና ሀገራዊ ፖለቲካዊ መረጋጋትን መገንባት ከተቻለ፣ የዓባይ ወንዝን ልማት ጨምሮ ሌሎች ታላላቅ ሀገራዊ ፕሮጀክቶችን በበለጠ አቅም ማስቀጠል እንደምትችልም ገልጸዋል።

አቶ ጁነይዲን ከኢቲቪ አፋን ኦሮሞ ጋር ባደረጉት ልዩ ቆይታ እንደተናገሩት፣ ግብፅ የተለያዩ ሴራዎችን በመጎንጎን፣ ኢትዮጵያ ወደ ቀይ ባሕር እንዳታቀና እና የባሕር በር እንዳታገኝ ለዘመናት ስትሠራ ቆይታለች፤ አሁንም ይኸው ሴራዋ አልተቀየረም።

ኢትዮጵያ ሰፊ ሀብት እና የልማት አቅም ያላት ሀገር መሆኗን በመጠቆም፣ አሁን ላይ የውስጥ ፈተናዎችን እና ልዩነቶችን ወደ ጎን በመተው ትኩረቷን ወደ ልማት ካደረገች፣ የታቀዱ ታላላቅ ሀገራዊ የልማት ግቦችን ማሳካት እንደምትችል አጽንዖት ሰጥተዋል።

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: