Search

የባዳ እና ባንዳ ተልዕኮን ለማክሸፍ በሚደረገው ጥረት የውስጥ አንድነትን ማጠናከር ያስፈልጋል፦ ምሁራን

ማክሰኞ ጥቅምት 17, 2019 58

ዓለም አቀፉ የሲቪል አቪዬሽን ድርጅት (ICAO) ባለፉት 14 ቀናት በኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ድርጅት በመገኘት አጠቃላይ የደኅንነት ኦዲት አድርጓል።

ድርጅቱ በግምገማው ያገኘውን ውጤት ያሳወቀ ሲሆን፣ በዚህም ኢትዮጵያ በሲቪል አቪዬሽን ደኅንነት ግምገማ አጠቃላይ የደኅንነት ኦዲት 85 ነጥብ 76 በመቶ ውጤት ማግኘቷን ይፋ አድርጓል።

ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የሲቪል አቪዬሽን የደኅንነት ቁጥጥር መስፈርቶችን በምን  ያህል ደረጃ እየተገበረች ነው የሚለውን የገመገመው ድርጅቱ፣ በግምገማው ህግና ደንብ አወጣጥ እንዲሁም ቁጥጥር፣ የደኅንነት ምርመራ፣ ፈቀድ አሰጣጥ የደኅንነት ጉድለቶችን ለማስተካከል የተሠሩ ሥራዎችን በደኅንነት ኦዲቱ ተመልክቷል።

የተገኘው ውጤትም ኢትዮጵያ ለበረራ ደኅንነት የሰጠችውን ትኩረት የሚያመላክት እና የበረራ ደኅንነት መረጋገጡን እንደሚያሳይ አመላክቷል።

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ዳይሬክተር ጀነራል ዮሐንስ አበራ የመደመር መንግሥት ለተቋማት ጥንካሬ የሰጠው ትኩረት ለተገኘው ውጤት በጎ አስተዋፅኦ ማበርከቱን ተናግረዋል።

ከ11 ዓመት በፊት በተደረገ የደኅንነት ኦዲት የተገኘው ውጤት 62 በመቶ እንደነበረ ያስታወሱት አቶ ዮሐንስ፣ አሁን የተገኘው ውጤት ለአቬሽን ዘርፍ በተሰጠው ልዩ ትኩረት ነው ብለዋል።

የተገኘው ውጤት በኢትዮጵያ የበረራ ደኅንነት የተረጋገጠ መሆኑን በማመላከት የአየር ትራንስፖርት ፍሰትን የሚጨምር እንደሆነም ተገልጿል።

በመስከረም ቸርነት

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: