የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) ምክትል ማኔጂንግ ዳይሬክተር ኒጌል ክላርክ፣ ኢትዮጵያ የማክሮ-ኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳዋን ወደፊት ለማራመድ ያሳየችውን ጥንካሬ፣ ጽናት እና ቁርጠኝነት አድንቀዋል።
ምክትል ማኔጂንግ ዳይሬክተሩ ይህንን ያሉት ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ኢዮብ ተካለኝ (ዶ/ር) ጋር ባደረጉት የሁለትዮሽ ውይይት ወቅት ነው።
ኢትዮጵያ የተጀመሩትን የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች ወደ ፊት ለማስኬድ የምታደርገውን የጸና ቁርጠኝነት እና የማያወላውል ጥረት እንዲሁም ያጋጠሟትን ፈተናዎች በመሻገር የኢኮኖሚ ማሻሻያ እንቅስቃሴውን ለማስቀጠል ያሳየችውን ቆራጥነት አድንቀዋል።
ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን አጋርነት ይበልጥ ለማጠናከር እና ለአጠቃላይ የኢኮኖሚ ትራንስፎርሜሽኑ የሚያደርገውን ቀጣይነት ያለው ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: