የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና ቻይና ሳውዘርን አየር መንገድ በቻይና እና በኢትዮጵያ መካከል በሚደረጉ ቀጥታ የበረራ አገልግሎቶች እንዲሁም በሁለቱ ሀገራት ክልላዊ የአየር ትራንስፖርት ገበያዎች ላይ ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር የሚያስችል የኮድሼር ስምምነት ተፈራርመዋል።
ይህ አጋርነት ደንበኞች የሁለቱንም አየር መንገዶች የበረራ መረብ በመጠቀም ወደ ተለያዩ የአፍሪካ እና የቻይና መዳረሻዎች ያልተቋረጠ እና ቀልጣፋ የጉዞ አገልግሎት እንዲያገኙ እንደሚያስችላቸው የኢትዮጵያ አየር መንገድ መረጃ አመላክቷል።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: