Search

ኢትዮጵያ የበለጠ ጠንካራ፣ ተወዳዳሪ እና በኢንቨስትመንት የሚመራ ኢኮኖሚ ለመገንባት ጽኑ ቁርጠኝነት አላት፦ ኢዮብ ተካለኝ (ዶ/ር)

ሓሙስ ጥቅምት 05, 2019 45

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ኢዮብ ተካለኝ (ዶ/ር)፣ በዓለም ባንክ እና በዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) ዓመታዊ ስብሰባ ጎን ለጎን “የሕይወት መስመር ከብድር በኋላ፦ ሀገራት ከቀውስ በኋላ እንዴት ማንሰራራት እና ማደግ ይችላሉ?” በሚል ርዕስ በFinance for Development Lab በተዘጋጀው ከፍተኛ የመሪዎች ውይይት መድረክ ላይ የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል።

ዶክተር ኢዮብ የኢትዮጵያን ተሞክሮ መሠረት በማድረግ ባደረጉት ንግግር፣ የብድር ጫናን እና ስጋትን መቅረፍ ለዘላቂ ኢኮኖሚያዊ ማንሰራራት የመጀመሪያው እርምጃ ብቻ መሆኑን ገልጸዋል።

አክለውም በወቅቱ የሚደረግ የብድር እፎይታ፣ ጠንካራ የአበዳሪዎች ቅንጅት እና ተዓማኒነት ያላቸው የማክሮ-ኢኮኖሚ ማሻሻያዎች ለአዳዲስ ኢንቨስትመንቶች እና ለዘላቂ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት በአስቸኳይ መንገድ መክፈት እንዳለባቸው አጽንዖት ሰጥተው ተናግረዋል።

ወደፊት የሚከናወኑ ተግባራትን አስመልክተውም፣ በማደግ ላይ ያሉ ሀገራት ከብድር ጫና ተላቅቀው ቅድሚያ የሚሰጧቸውን የልማት ተግባራት በዘላቂነት በፋይናንስ ማደራጀት እንዲችሉ የበለጠ ፈጣን ምላሽ የሚሰጥ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሥርዓት እንዲገነባ ጥሪ አቅርበዋል።

ኢትዮጵያ የበለጠ ጠንካራ፣ ተወዳዳሪ እና በኢንቨስትመንት የሚመራ ኢኮኖሚ ለመገንባት ጽኑ ቁርጠኝነት ያላት መሆኑንም አረጋግጠዋል።

#የመደመርመንግሥት

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: