Search

ኢትዮጵያ ጠንካራ የIMF አጋርነት እና ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሥርዓት ማሻሻያ እንዲደረግ ጥሪ አቀረበች

ሓሙስ ጥቅምት 05, 2019 37

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ኢዮብ ተካለኝ (ዶ/ር) በባንኮክ ታይላንድ ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) ማኔጂንግ ዳይሬክተር ክሪስቲሊና ጂዮርጂቫ ጋር በተካሄደው ከፍተኛ የአፍሪካ ካውከስ እና የባንክ ገዥዎች ስብሰባ ላይ ባደረጉት ንግግር፣ በማዕበል እና አደጋዎች የማይናጋ የኢኮኖሚ ዕድገትን ለማረጋገጥ አዳጊ ሀገራት የጠለቀ ዓለም አቀፍ አጋርነት እና ሥርዓታዊ ማሻሻያዎች እንደሚያስፈልጓቸው ገልጸዋል።

ዶክተር ኢዮብ በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳ ሥር የሚገኘውን የኢትዮጵያን አጠቃላይ ጉዞ በማስመልከት በሰጡት ማብራሪያ፣ በጥናት እና በታቀደ መንገድ የተወሰዱት ሀገር በቀል የፖሊሲ ማሻሻያ ውሳኔዎች ኢኮኖሚውን በተሳካ ሁኔታ ማረጋጋታቸውን እና አዳዲስ የዕድገት አድማሶችን መክፈታቸውን ጠቁመዋል።

የአፍሪካን የኢኮኖሚ አቅም ወደ ዘላቂ ዕድገት ለመቀየር፣ የአፍሪካ ሀገራት የባንክ ገዥዎች አህጉሪቱ በመዋቅራዊ ማሻሻያዎች፣ በፈጠራ እና በቀጣናዊ ትሥሥር አማካኝነት በራሷ አቅም የምታመጣውን ትራንስፎርሜሽን ለማረጋገጥ ያላቸውን ቁርጠኝነት ገልጸዋል።

የአፍሪካ ካውከስ መድረኩም ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት ከአፍሪካ ታላላቅ የልማት ቅድሚያዎች ጋር እኩል በመራመድ አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርጉ በጽኑ በመጠየቅ ተጠናቅቋል።

#የመደመርመንግሥት

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: