Search

ኢትዮጵያ ከዓለም አቀፍ የፋይናንስና የቴክኖሎጂ ተቋማት ጋር ያላትን ስትራቴጂያዊ አጋርነት አጠናከረች

ሰኞ ጥቅምት 09, 2019 52

ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂ፣ በልማት እና በባንክ ዘርፎች ከሚንቀሳቀሱ ግንባር ቀደም ዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር ያላትን የፋይናንስና የኢኮኖሚ አጋርነት ይበልጥ ለማጠናከር የሚያስችሉ ስትራቴጂያዊ ውይይቶችን አካሂዳለች።

በብሔራዊ ባንክ ገዥ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) የተመራው ከፍተኛ የኢትዮጵያ ልዑክ ከዓለም አቀፉ የክፍያ ቴክኖሎጂ ኩባንያ ቪዛ፣ ከጣሊያኑ የመንግሥት የልማት ባንክ ካሳ ዲፖዚቲ ኤ ፕሬስቲቲ (CDP) እና ከባንክ ኦፍ አሜሪካ አመራሮች ጋር ተከታታይ የሁለትዮሽ ውይይቶችን አድርጓል። 

ውይይቶቹ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትን ለማፋጠን፣ የዲጂታል ፋይናንስ መሠረተ ልማትን ለማጠናከር፣ የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋም የልማት ፋይናንስ መሠረት ለማስፋት እና ኢትዮጵያን ከዓለም አቀፍ የንግድ ባንክ መረቦች ጋር ይበልጥ ለማስተሳሰር ያለሙ መሆናቸው ተገልጿል።

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: