የኢትዮጵያ መንግሥት በሀገር ሉዓላዊነት እና ደኅንነት ላይ አደጋ በሚደቅኑ ተገንጣይና አሸባሪ ኃይሎች ላይ እየወሰደው ያለው የሕግ ማስከበር እርምጃ ተገቢና ሕጋዊ መሆኑን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ገልጸዋል።
ማርኮ ሩቢዮ በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች የሚንቀሳቀሱ ታጣቂ ኃይሎች የሽብር ድርጊት መፈጸማቸውን ገልጸው፤ የኢትዮጵያ መንግሥት ለተደቀነው ስጋት የሰጠው ምላሽ ተገቢ ስለመሆኑ በአጽንኦት ተናግረዋል።
ሚኒስትሩ በሰጡት ይፋዊ መግለጫ፣ በኢትዮጵያ ላይ ጥቃት ያደረሱ ተገንጣይ ኃይሎች መኖራቸውን በመጥቀስ፤ የኢትዮጵያ መንግሥት ለነዚህ አካላት የሰጠው ምላሽ እና እየወሰደው ያለው የአጸፋ እርምጃ ሀገራዊ ሉዓላዊነትን ለማስከበር የሚደረግ በመሆኑ ተገቢነት ያለው ነው ሲሉ ገልጸዋል።
አያይዘውም ግጭቱ ወደ ጎረቤት ሀገራት እንዳይዛመት አሜሪካ ከኢትዮጵያ ጋር እንደምትሠራ ገልጸው፤ አሸባሪነት በግልጽ ሊወገዝ የሚገባው ተግባር መሆኑን አስምረውበታል።
ኢትዮጵያ በሀገሯ ውስጥ የውክልና ጦርነት በከፈቱባት ቡድኖች ላይ የምትወስደውን የሕግ ማስከበር እርምጃ አሜሪካ እንደምትደግፍ እና ለዚህም ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር በቅርበት እንደምትሠራ አረጋግጠዋል።
ሕገ-ወጡ የህወሓት ቡድን በፕሪቶሪያው ስምምነት መሠረት ሙሉ በሙሉ ትጥቅ ከመፍታት ይልቅ ሂደቱን ለማጓተት መሥራቱ፣ ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱን ለመናድ ዳግም መነሳቱ እንዲሁም ለተቸገረው የትግራይ ሕዝብ የሚላከውን ሰብዓዊ እርዳታ ለታጣቂዎቹ ቀለብ ማዋሉ በምርመራ መረጋገጡ የምዕራባውያንን እና የለጋሽ ሀገራትን እምነት እንዲያጣ አድርጎታል።
በሃና ምንዳሁን
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: