Search

ኢትዮጵያ ባላት የሰው ኃይል የማይበገር እና ራሱን የቻለ የአፍሪካ የጤና ሥርዓት ለመገንባት ቁርጠኛ ነች፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ሰኞ ኅዳር 14, 2019 34

ኢትዮጵያ ባላት የሰው ኃይል፣ በሀገር ውስጥ የመድኃኒት ምርት፣ በዲጂታል ጤና እና በሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) ላይ ኢንቨስት በማድረግ የማይበገር እና ራሱን የቻለ የአፍሪካ የጤና ሥርዓት ለመገንባት ቁርጠኛ መሆኗን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአፍሪካ የበሽታዎች መቆጣጠሪያና መከላከያ ማዕከል (Africa CDC) እና በኢትዮጵያ መንግሥት ትብብር በአዲስ አበባ በተዘጋጀው የ5ኛው የአፍሪካ የሕዝብ ጤና ኮንፈረንስ (CPHIA 2026) መክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ ንግግር አድርገዋል።

በባህላችን ሰላምታ የመልካም ጤንነት ምኞት ነው፤ በዚህም መንፈስ የአፍሪካ ኅብረት እና የአፍሪካ ሲዲሲ መቀመጫ ወደሆነችው አዲስ አበባ እንኳን ደህና መጣችሁ ለማለት እወዳለሁ ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)  የበመደመር እሳቤ በመመራት የጤና መዋቅሩ በሦስት ዋና ዋና ቅድሚያ በሚሰጣቸው ጉዳዮች ዙሪያ መለወጥ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

እነሱም የሕክምና ልህቀት ማዕከላትን መገንባት፣ የአፍሪካ አምራቾችን ለማብቃት በጋራ ግዥ መፈጸም እንዲሁም በታካሚዎች ጤና ላይ ተጨባጭ ለውጥ ለማምጣት ጥብቅ ተጠያቂነትን ማረጋገጥ መሆናቸውን አመላክተዋል።

ኢትዮጵያ በቀጣይ ዓመት የምታስተናግደውን 32ኛ የተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ COP32 እንዲታደሙም ለተሳታፊዎቹ የክብር ግብዣ አቅርበዋል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: