Search

ሀገር እና ተቋም የሚረከበው ተተኪ መኮንን ፕሮፌሽናሊዝምን በመላበስ አመርቂ ግዳጅ እየፈጸመ ይገኛል፦ ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ

ቅዳሜ ሰኔ 06, 2018 338

‎የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ለመጠበቅ የተዘጋጀ ወታደራዊ አመራር ዓለም አቀፉዊ፣ አህጉራዊ እና ቀጣናዊ ጉዳዮችን በመረዳት፣ የሚመራውን አሀድ ሥነ ልቦናዊ ዝግጁነት ማረጋገጥ እንደሚባው የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ ገለጹ።

‎

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የማዕከላዊ ዕዝ መኮንኖች በግዳጅ አፈጻጸምና ቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ የጋራ መግባባት በያዙበት መድረክ በቪድዮ ኮንፈረንስ ማጠቃለያ ሰጥተዋል።

‎

‎መኮንኑ የጦሩን የዕለት ተለት ውስጣዊ አቅሞች በመፈተሽ ድል የሚፈጥር የሀገር ባለውለታ መሆኑን ያወሱት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ፤ ሀገር እና ተቋም የሚረከበው ተተኪ መኮንን ፕሮፌሽናሊዝምን በመላበስ አመርቂ ግዳጅ እየፈጸመ ይገኛል ብለዋል።

‎

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የድል አድራጊነቱ ምስጢር ዲሲፕሊኑ መሆኑን በማንሳትም፣ መኮንኑ አርዓያ በመሆን የሚያጋጥሙትን ፈተናዎች ሁሉ በብቃት ለመወጣት ዝግጁ ሊሆን እንደሚገባ መናገራቸውን ከኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ማኅበራዊ ትስስር ገፅ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

‎

‎የማዕከላዊ ዕዝ አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ዘውዱ በላይ በበኩላቸው፣ ተቋሙ በተለያዩ ኮርሶች የሚያሰለጥናቸው መስመራዊ መኮንኖች ከቴክኖሎጂ ጋር የተግባቡ በመሆናቸው ተልዕኮን በአጭር ጊዜና በአነስተኛ ኪሳራ የመፈጸም ብቃታቸው ከፍ ያለ ነው ብለዋል።

‎

ዕዙ ለማንኛውም ስምሪት አጋዥ የሆኑ የሠራዊት ግንባታ አቅጣጫዎችን በብቃት በማለፍ ለድል አስተማማኝ ቁመና ላይ እንደሚገኝ አረጋግጠዋል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: