ዲላን ፔጅ (Dylan Page) በመባል የሚታወቀው የዲጂታል ጋዜጠኛ እና የማህበራዊ ሚዲያ ይዘት ፈጣሪ በኢንስቲትዩቱ በመገኘት የተቋሙን ሥራዎች ተመልክቷል።
ዲላን ጉብኝቱን አስመልክቶ በሰጠው አስተያየት፣ “ይህ ጉብኝት በዓለም አቀፍ ደረጃ ስለ አፍሪካ ያለውን የተዛባ አመለካከት የሚቀይር ነው” ብሏል።
“ይህን በቴክኖሎጂ የተቃኘ ቦታ ሳየው ተደምሜያለሁ፣ በጣም ያማረና አስደናቂ ቦታ ነው፤ አፍሪካ ተቀይራለች፣ አዲሱን ገፅታዋን ለዓለም የሚያሳይ ቦታ ሆኖ አግኝቼዋለሁ” ሲል ገልጿል።
ዲላን በፈጣን አቀራረብ፣ አጭር፣ ሳቢ እና ለመረዳት ቀላል የሆኑ ዓለም አቀፍ ዜናዎችን እና ወቅታዊ ሁኔታዎችን በተለይም ለወጣቶች በሚመች መልኩ በማቅረብ ይታወቃል።
በቲክቶክ ከ19 ሚሊዮን በላይ ተከታዮች ያሉት ዲላን፣ በራሱ ልዩ የአቀራረብ ዘይቤ ዓለም አቀፍ ተከታዮችን ማፍራት የቻለ ሲሆን፤ በተለይም ወጣቱ ትውልድ ዜናን የሚቀበልበትን መንገድ በመቅረጽ ረገድ ትልቅ ሚና እየተጫወተ ይገኛል።
#Ethiopia #AddisAbaba #ArtificialIntelligence #DylanPage #EBC